ሰንደቅ አላማችን ለብሄራዊ መግባባታችንና ለአንድ...

image description
image description
image description
image description
- Events info news    0

ሰንደቅ አላማችን ለብሄራዊ መግባባታችንና ለአንድነታችንǃǃǃ

የአዲስ አበባ ከተማ ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች “ሰንደቅ አላማችን ለብሄራዊ መግባባታችንና ለአንድነታችን!” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን ብሄራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን አክብረዋል።

በበዓሉ አከባበር ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ ሰንደቅ አላማ የታሪክ፣ የሉአላዊነት እና የህብረብሄራዊ አንድነት መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከሀገር መገለጫነት አልፎ ለመላው ጥቁር ህዝብ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት መሆን የቻለ አርማ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አውስተዋል።

አገራዊ ከፍታን ለማረጋገጥ መግባባት ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ ልዩነቶቻችንን በመግባባት በመፍታትና አንድነታችንን በማጠናከር የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ ከፍ ማድረግ አለብን ብለዋል።

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በበኩላቸው በስነ-ምግባርና በስራ ወዳድነት የሰንደቅ አላማውን ከፍታ ለማረጋገጥና ሀገራዊ አደራቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments