ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም...

image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች እውቅና ሰጠ።

ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች እውቅና ሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2018 በጀት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የእውቅና መርሃ ግብር አካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ  ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን  ኮሚሽነር  ጀማል ረዲ  በበጀት ዓመቱ ከግንዛቤ ፈጠራና ማስተማር ሥራዎች ጎን ለጎን የሙስና ጥቆማዎችን በመከታተልና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ገልፀዋል።

አክለውም ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮችን በመፈተሽና ተጠያቂነትን በማስፈን ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ አሰራር  እንዲዘረጋ   አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

 የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት በሆኑት በስነ ምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል ረገድ በበጀት ዓመቱ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በምዘና ሂደት በመለየት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ክፍሎች እውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር  መቅደስ ተስፋዬ  ገልፀዋል። አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ መከታተያ ክፍሎችም ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲመጡ በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ኮሚሽነሯ ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር  ሀብታሙ ፈይሳ የሙስና መከላከል ሥራውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ እንደሚገባ በመናገር  በቀጣይ የሀብት ምዝገባን በዘመናዊ ሶፍትዌር ሲስተም በመተግበር ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት እና ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አመርቂ ለውጥ ለማስመዝገብ መታቀዱን ጠቁመዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments