ኮሚሽኑ ለሀረሪ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ልምዱን አካፈለ፡፡
ኮሚሽኑ ለሀረሪ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ልምዱን አካፈለ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለሀረሪ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ልምዱን አካፍሏል፡፡
በልምድ ልውውጡ የኮሚሽኑ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቱ ሰማን ኮሚሽኑ በቅርቡ የተቋቋመ ቢሆንም በስነ-ምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል ረገድ ግንባር ቀደም መሆን የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችንና ማንዋሎችን በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባቱን ያነሱት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የደረሰበትን አጠቃላይ አደረጃጀትና የትውልድ ስነምግባር ግነባታና የሙስና መከላከል ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከሀረሪ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የመጡት የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች በበኩላቸው፤ ከአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የወሰዱት ልምድ ለተቋም ግንባታና ለሙስና ትግሉ አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም በስነ-ምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል ረገድ በተሞክሮ የሚቀመሩ በርካታ አሰራሮችን መቅሰማቸውን አረጋግጠዋል።
በልምድ ልውውጥ ሂደቱ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ የስልጠና፣የግንዛቤ ፈጠራና የፀረ-ሙስና ትምህርት አሰጣጥ ስራዎች፤ በሙስና መከላከል ስራዎች የጥቆማ አቀባበልና አፈታት ሥርዓት፣ የሙስና መከላከል ጥናትና የትግበራ ክትትል ግምገማ፣ እንዲሁም የሀብት ምዝገባ አፈጻጸም ተቃኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የበለጸጉ ዘመናዊ የዲጂታል አሰራሮች ልምድ ተወስዶባቸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments