ሀብትን የማስመዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ በማስደገፋችን በሀገር ደረጃ ለሌሎች ክልሎች ልምድ እስከማካፈል ደርሰናል።
ሀብትን የማስመዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ በማስደገፋችን በሀገር ደረጃ ለሌሎች ክልሎች ልምድ እስከማካፈል ደርሰናል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በሲስተም የተደገፈ የሀብት ምዝገባ ስልጠና በአምስት ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የወረዳ ስነ ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዘገየ በላይነህ እንደገለፁት ሀብትን በሲስተም መመዝገብ መጀመራችን የሀብት ምዝገባ ስርዓቱን ሚስጥራዊ እንዲሆን ከማድረጉ ባሻገር በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜና በጥቂት የስው ኃይል ማስመዝገብ ያስችላል ብለዋል።
አያይዘውም ሀብትን የማስመዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ በማስደገፋችን በሀገር ደረጃ ለሌሎች ክልሎች ልምድ እስከማካፈል መድረሱን አመልክተዋል።
የኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባና ጥቅም ግጭት ማስወገድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ቅድስት ይበልጣል በበኩላቸው የሀብት ምዝገባ ሲስተሙ አዋጅ ቁጥር 668/2002 መሰረት ተደርጎ የለማ ሲሆን ከዚህ ቀደም በወረቀት የነበረውን የተንዛዛ የምዝገባ ስርዓት ያስቀረ መሆኑን አብራርተዋል።
"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments