"በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት፤ለሃገር ልማት በማ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

"በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት፤ለሃገር ልማት በማዋል በኩል ረጅም መንገድ መጓዝ ችለናል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት፤ለሃገር ልማት በማዋል በኩል ረጅም መንገድ መጓዝ ችለናል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

በዛሬዉ እለት 22ኛዉ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ከተማ አቀፍ ንቅናቄ የማጠቃለያ መደረክ አድዋ በሚገኘዉ ፓንአፍሪካ አዳራሽ  ተካሂዷል።

 

ኮሚሽኑ "ትዉልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ሃሳብ በየደረጃው ተቋማት በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር የቆየ ሲሆን የዛሬዉም ከተማ አቀፍ በዓል ተዘጋጅቷል፡፡

 

በከተማ አቀፍ መድረኩ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ሙስና ፀያፍ የሆነ፤ የሃገርን ገፅታ የሚገታ፤ ትዉልድን የሚጎዳ እና ኢ-ፍትሃዊነትን የሚያነግስ ተግባር በመሆኑ የመላዉ ማህበረሰብን እና የሁሉንም ተቋማት ትግል የሚጠይቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት በወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም፤ በተሰራዉ ስራ እና በተፈጠሩ አስቻይ ሁኔታዎች ሙስናን በመከላከል በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት ለሃገር ልማት በማዋል በኩል ረጅም መንገድ መጓዝ ችለናል ብለዋል፡፡፡

 

አክለዉም ሁልጊዜ በምንሰራዉ ስራ ሙስና እንዳይተገበር መከላከል ብቻ ሳይሆን ሙስናን  የሚፀየፍ ትዉልድ መገንባት ላይ ስለመሆናችን ራሳችንን መጠየቅ እና ከምንናገረዉ ባሻገር ሁነን መገኘት ትዉልድ እንዲከተለን የሚያደርግ እዉነታ ስለሆነ ይህን መርህ በጥብቅ ልንተገብረዉ ይገባል ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

 

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው የሙስና ትግሉ ትርጉም ያለው ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው በስነ ምግባር በታነፁ ዜጎችና በጠንካራ ተቋማት ሲታጀብ መሆኑን ገልፀው ግንዛቤ በመፍጠር የከተማዋ ማህበረሰብ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል ነው፡፡

ከተማችን ከመሠረተ ልማት እምርታ፣ አገልግሎትን ዲጂታላይዜ ማድረግ፣ ከማህበራዊ ልማት እስከ ተቋማዊ ለውጥ ዕድገቷ የሚታይና የሚለካ እንዲሆን ያስቻለውም በፀረ ሙስና ትግሉ በግንባር ቀደምትነት መጋፈጥ በመቻሏ መሆኑን ኮሚሽነር ጀማል አብራርተዋል፡፡ 

 

በከተማ አቀፍ መድረኩ  ላይ በከተማዋ በተደረገዉ  ንቅናቄ የፀረ-ሙስና ትግል ላይ የላቀ አስተዋፅአ ላበረከቱ ተቋማት እውቅና ተሰጧል::

ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments