ከለውጡ በኋላ ከተማ አስተዳደሩ በሙስና ላይ በያ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Events info news    0

ከለውጡ በኋላ ከተማ አስተዳደሩ በሙስና ላይ በያዘው  ፅኑ አቋም በርካታ ስኬቶች  መመዝገባቸው ተገለፀ፡፡

ከለውጡ በኋላ ከተማ አስተዳደሩ በሙስና ላይ በያዘው  ፅኑ አቋም በርካታ ስኬቶች  መመዝገባቸው ተገለፀ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር 22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ  የፓናል ውይይት አካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ ከለውጡ በኋላ ከተማ አስተዳደሩ በሙስና ላይ በያዘው  ፅኑ አቋም በርካታ ስኬቶች  መመዝገባቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ  ክቡር አቶ ማሾ ኦላና ከለውጡ በኋላ ከተማ አስተዳደሩ በሙስና ላይ ፅኑ አቋም በመያዝ የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው  በዚህም በርካታ የትውልድ ስነ ምግባር  ግንባታና የሙስና መከላከል ተግባራት መሰራታቸውን  ተናግረዋል። 

ሁሉም የህብረተሰብ በተለይም የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በምግባርም  በተግባርም አርአያ መሆን ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዋና ተጠሪው ሙስና በመቅረፍ  ብሎም ለከተማችን ልማት በመስራት ሀገራዊና ከተማዊ ለውጥ ማምጣት ይጠበቃል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው የፀረ ሙስና ቀን በተለያዩ የንቅናቄ መድረኮች ሲከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተቀራረበ እውቀት ኖሮት በጋራ የሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በመሆኑ ዓመቱን በሙሉ በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና የተቋማት አሰራር ስርዓት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሄር  በመንግስት አሰራር ላይ ሙስና  የመከላከል ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አንስተው  ኮሚሽኑ ለከተማችን ብሎም በሀገር አብነት ሊሆኑ የሚችሉ ውጤታማ  የሰነምግባር  ግንባታና የሙስና መከላከል ስራዎች መሰራቱን ጠቁመዋል።

ኃላፊው አክለውም ዘመኑ ያመጣውን የቴክኖሎጂ አሰራር በመጠቀም ሙስናን በመከላከል የከተማችንን ልማትና እድገት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተጋበዙ ምሁራን በእለቱ ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ አቅርበዋው በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገ ሲሆን ለኮሚሽኑ ቀጣይ ስራዎች አቅም የሚሆኑ ሀሳቦች የተገኙበት መድረክ መሆኑ ተጠቀሟል።

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments