"ሙስናና ብልሹ አሰራሮች አምርሮ የሚታገል ትው...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

"ሙስናና ብልሹ አሰራሮች አምርሮ የሚታገል ትውልድ ለመፍጠር እየተስራ ነው" ፍቃዱ ሰቦቃ የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

"ሙስናና ብልሹ አሰራሮች አምርሮ የሚታገል ትውልድ ለመፍጠር እየተስራ ነው"

 

ፍቃዱ ሰቦቃ

የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

                

ህዳር 21 ቀን 2018 አ/አ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ ምግባር ፀረ-ሙና ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ከተማ ወጠቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር 22ተኛውን ዓለም ዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን  "ትውልድን በስ-ነምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ  አክብረዋል፡፡

 

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተገኙት የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ እንደገለፁት   ሙስናን ለመከላከል የወጣቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቱን  በመልካም ስነ ምግባር በመገንባት ሙስናና ብልሹ አሰራሮች አምርሮ የሚታገል

ትውልድ ለመፍጠር እየተስራ ነው ብለዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን መልካም ስነ ምግባር ያላቸውን ወጣቶች ለማፍራት በትምህርት ቤቶች ክበባትን በማደራጀት እየሰራ ያለው ሥራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ከኮሚሽኑ ጎን በመቆም ሙስናን መታገል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ ምግባር ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው ሙስና አለም አቀፍ የጋራ ጠላት በመሆኑ በጋራ ለመታገል እንዲያስችል አለም አቀፍ የፀረ - ሙስና ቀን በተለያዩ መሪ ቃሎች እየተከበረ ይገኛል። የዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን ከወጣቶች ጋር ስናከብር የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናችሁ ወጣቱን በመልካም ስነ ምግባር መገንባት ተቋምን ከመገንባት ባሻገር ሀገርን መገንባት ነው ብለዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ ሙስናና ብልሹ አሠራርን የሚፀየፍና የሚታገል በአካልም በስነ ምግባር የበለፀገ ትውልድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

 

22ተኛው ዓለም ዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በየደረጃው በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

 

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments