ኮሚሽኑ በ2017 በጀት አመት የተሻለ ስራ ስራ...

image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

ኮሚሽኑ በ2017 በጀት አመት የተሻለ ስራ ስራ አፈፃፀም ላመጡ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች እውቅና ሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን  በ2017 በጀት አመት የተሻለ ስራ ስራ አፈፃፀም ላመጡ  የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች የእውቅና ሽልማት መርሀግብር አካሄደ ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ተቋሙ በበጀት አመቱ በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታእና በሙስና መከላከል የነበረውን የስራ እንቅስቃሴ የነበሩ ጉድለቶችን በማረም ጥንካሬዎችን በማጎልበት  ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል።

በበጀት አመቱ የተሻለ  አፈፃፀም  ላመጡ  የኮሙሽኑ መከታተያ ክፍል እውቅና መስጠቱ ለቀጣይ መከታተያ ክፍሎች ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ የስራ ተነሳሽነትን የሚያጎለብት መሆኑን ተናግረዋል ።
አያይዘውም ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል ሁሉም በኮሚሽኑ ያሉ ተቋማት በትጋት መስራት  እንዳለባቸው ኮ/ሩ አሳስበዋል።


በ 2017 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ ለነበረው የስራ አፈፃፀም ውጤታማነት  ሁሉም መከታተያ ክፍሎች  ከፍተኛ ሚና መወጣታቸውን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ  ገልፀዋል።
አክለውም  የቀጣይ ስራዎችን በምን መልኩ እንደምንሰራ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰን በሙሉ ሀይል መስራት ይገባል  ብለዋል።

በመርሀግብሩ በ2017 በጀት አመት አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ያመጡ የሴክተር ተቋማት፣ የሆስፒታሎች፣ የኮሌጆች፣ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች፣ የክፍለ ከተሞች እና የወረዳዎች የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

በተጨማሪም የ2017 በጀት ዓመት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት፤የ 2018 በጀት አመት የኮሚሽኑ  እቅድ እና ለመከታተያ ክፍሎች ካስኬድ የደረገ እቆድ  የኮሚሽኑ እቅድና በጀት ባለሙያ አቶ ግዛቸው ደገፉ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments