በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች...

image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ለአመራርና ሰራተኞች በስነ-ምግባርና ብልሹ አሰራር ዙራያ ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው የተገኙት የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተርና የመስሪያ ቦታ አስተዳደርና ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መርቆ ብርሌው ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በተገነባ አቅምና በኤጀንሲው ደንብ ተመርቶ ማረም ይገባል ብለዋል፡፡ሰልጣኞች ባገኙት ስልጠና ተነሳስተው ተገልጋዩን ህብረተሰብ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ይኖርባቸዋል ሲሉ አቶ መርቆ ተናግረዋል፡፡የኤጀንሲው የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ከተማ ተገኑ በስነ-ምግባርና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል።በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ሰልጣኞች ግልፅነት ቢፈጠርባቸው ያሏቸው ግዳዮችን አንስተው ከቤቱና ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡በስልጠናው የማዕክል ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የሁሉም ክ/ከተማ የጽ/ቤት አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments