


#በመትከልማንሰራራት
#በመትከልማንሰራራት
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም የአ/አ/ከ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ዙር እየተከናወነ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አሻራቸውን አኑረዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ ግብር ከመትከል በዘለለ የሚተከሉ ችግኞች እንደየአየር ጠባዩና የአፈር ሁኔታው ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንደ ኮሚሸን ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ ተሳትፎ አድርገናል ያሉት ኮሚሽነሩ የምንተክላናቸውን ችግኞች በየጊዜው በመንከባከብ ጭምር ሊሆን ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች በዛሬው እለተ ሀገር በቀል የሆኑ ዛፎችን መትከላቸው ተገልጿል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments